Menu Close

እንኳን ደስ አለን/ደስ አላችሁ!!!!!


በቸሻየር ኢትዮጵያ-ሀዋሳ ተሃድሶ ማዕከል የሚሰጠው የአካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያደርሰው የታመነበት እና አካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ፈልገው ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ማዕከላችን ለሚመጡ አካል ጉዳተኞች ጊዜያዊ የመኝታ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ግንባታ ተጠናቆና አስፈላጊ ግብዓቶች ተሟልተውለት በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡


በግንባታው ምረቃ ስነ-ስረዓት ላይ የተለያዩ የድርጅታችን የስራ ሃላፊዎች፣ የድርጅታችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሃላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የድርጅታችን ተጠቃሚዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል፡፡
የምረቃ መርዓ-ግብሩን በይፋ ያበሰሩት የድርጅታችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር ግርማ አባቢ (የሊያና/ያኔት ሄልዝ ኬር መስራችና ባለቤት) እንደተናገሩት የዚህ ጊዜያዊ የመኝታ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ግንባታ አካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት ፈልገው ከተለያዩ አካባቢዎች ወደ ማዕከሉ ለሚመጡ አካል ጉዳተኞች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን በተለይም በማዕከሉ የሚሰጠውን አካላዊ ተሃድሶ አገልግሎት የተሟላ፣ የተጠቃሚዎችን የኢኮነኖሚ ችግር የሚፈታ፣ ደህንነታቸው እና ምቾታቸው ተጠብቆ የሚቆዩበት የመኝታ ክፍሎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡


ከዚህም በተጨማሪ የቸሻየር ኢትዮጵያ ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር አቶ ፋሲል አየለ እንደተናገሩት የአካል ጉዳተኞች ቁጥር እያሻቀበ የመጣ ሲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመተባበር ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ የሆነ ሁለንተናዊ የተሃድሶ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልፀው በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቃው የመኝታ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ግንባታ ድጋፍ ላደገሩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Posted in blog

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *