Menu Close

ድጋፍ በምናደርግላቸው አካል ጉዳተኞች ስም ከልብ እናመሰግናለን!!!!!

የሲዳማ ክልል ማህበረሰብ አቀፍ ጤና ስፖርት ማህበር እና በስሩ የሚገኙ የጤና ስፖርት ማህበራት ላደረጋችሁልን የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን!!!!!!!!!!

ህብረተሰቡ በመረጠው የስፖርት አይነት እንቅስቃሴ እያደረገ ራሱን ተላላፊ ካልሆኑ በሽታዎች እንዲጠብቅ ማህበረሰብ አቀፍ ጤና ስፖርቶችን እንዲመራ በአዲስ መልክ የተቋቋመው የሲዳማ ክልል ማህበረሰብ አቀፍ ጤና ስፖርት ማህበር በተቋቋመ ማግስት ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጎን ለጎን የተለያዩ በጎ ተግባራትን ማከናወን እና ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት ጀምሯል፡፡

ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ የክልላችን መዲና በሆነችው ሀዋሳ ከተማ ውስጥ በርካታ የጤና የእግር ኳስ ስፖርት ማህበራት ተቋቁመው ስፖርታዊ ውድድሮችን በማድረግ ጤንነታቸውን ከመጠበቅ ባለፈ የእግር ኳስ ስፖርትን በማነቃቃት ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዎ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

ታዲያ በሁሉም የጤና ስፖርት ማህበራት ውስጥ የሚገኙ አባላት/ስፖርተኞች በተለያዩ የሙያ መስክ ተሰማርተው የሚገኙ ወጣቶች ሲሆኑ በትርፍ ጊዜያቸው በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ጤናቸውን ከመጠበቅ በተጨማሪ ማህበራዊ ሃላፊነቶቻቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ፡፡

Posted in blog, News

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *