እየተዝናኑ ታላቅ አላማን ይደግፉ
እየተዝናኑ ታላቅ አላማን ይደግፉ
የቸሻየር ኢትዮጵያ 60ኛ ዓመት የምስረታ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በድርጅቱ የተሃድሶ ማዕከላት ማለትም በሐዋሳ እና በሐረር የገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ጉዞ የተደረገ ሲሆን በድሬዳዋ በቅርቡ ለማድረግ ዝግጅቱ ተጠናቋል። የዚህ ዝግጅት ማጠቃለያ የሆነው መርሃ ግብር ሚያዝያ 28, 2015 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ይኸውም ከመናገሻ ተሃድሶ ማዕከል ተነስቶ ወደ መናገሻ ከተማ ደርሶ መልስ የ 10 ኪ.ሜ የእግር ጉዞ ተዘጋጅቷል። ታድያ እናንተም ዘንድሮ ለ45ኛ ጊዜ በሚካሄደው ታሪካዊ የእግር ጉዞ ላይ በመሳተፍ ከአካል ጉዳተኞች ጎን እንድትቆሙ ተጋብዛችኋል።