ቸሻየር ኢትዮጵያ ሀዋሳ ማዕከል የድርጅቱን ዓመታዊ ስብሰባውን አስመልክቶ የካቲት 17, 2015 ዓ.ም ሀዋሳ ማዕከል በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ፡፡ በዕለቱ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፋሲል አየለ አጠቃላይ የሀዋሳ ማዕከል ስራ አፈጻጸም የተሻለ እንደሆን ጠቅሰው ማህበረሰቡን ከዚህ የበለጠ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል አጠናክረው ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ ለሰራተኞቹ ገልጸዋል፡፡ የድርጅቱ የሰው ሃብትና ሎጅስቲክ ዳሬክተር አቶ የስጋት አሳየ ተሻሽሎ የጸደቀውን መተዳደሪያ ደንብና የሰራተኞች ከላላ እና ጥበቃን አስመልከተው ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከሰራተኞቹ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡



