Menu Close

ቸሻየር ኢትዮጲያ በዲላ ከተማ

ቸሻየር ኢትዮጲያ በዲላ ከተማ እየተገበረ በሚገኝው የ”Work and Respect Project” አማካኝነት “Dilla town lobby and Advocacy group” የዲላ ከተማ አግባቦት/ማሳመን እና መሞገት” ቡድንን በማቋቋም ለአካል ጉዳተኞች መብት መከበር የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ የአካል ጉዳት የገጠማቸው ወገኖች በተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ገብተው ለመስተናገድ ሲቸገሩ ይታያል፡፡ ታዲያ ይህንንና የመሳሰሉ ችግሮች ላይ ተገቢው እርምት እንዲወሰድ ለማስቻል ይህ ቡድን ከባለፍው አንድ አመት ወዲህ የተለያዩ የልማት ስራዎችን በቡድና በግል ሲሰራ የቆየ ውጤታማ ቡድን ነው፡፡
ታዲያ ዛሬ አንዲት ስኬታማ፣ጎትጓችና አሳማኝ ሴት የሰራችውን መልካም ተግባር ተሞክሮ ስራ ይዤ መጣው፤ ስሟ ወ/ሮ መነን አሰፋ ትባላለች መኖሪያ አድራሻዋ ዲላ ከተማ ሲሆን የገጠማት አካል ጉዳት አይነት የእግር ሲሆን ዊልቸር ተጠቃሚ ናት፤ ታዲያ ይህ ሁሉ ሳይበግራት የተለያዩ የንግድ ስራዎችን በመስራት በስኬታማነቷ በግባር ቀደም ከሚጠቀሱ ጠንካራ ሴት አካል ጉዳተኞች ውስጥ አንዷ ናት፡፡ ለብዙዎችም በአርአያነት የምትጠቀስ ናት፡፡ የዲላ ከተማ “lobby and Advocacy” ወይም በአማርኛ ”ማግባባት/ማሳመን እና መሞገት” ቡድን ከተቋቋመበት ግዜ ጀምሮ በአባልነት እንዲሁ የስራ አስፈጻሚ አባል በመሆን የተለያዩ በጎ ተግባራትን ስትፈጽም ቆይታለች፡፡

በዲላ ከተማ የሚገኙ አገልግሎት ሰውጪ ተቋማት በሌሎች ከተሞች ውስጥ እንደሚታየው የአካታችነት ቸግር/ውስንነት ከሚታይባቸው አንዱ ነው፡፡ ታዲያ ወ/ሮ መነን የባንክ አገልግሎት ለማግኘት በዲላ ከተማ የሚገኘው አቢሲኒያ ባንክ ለመስተናገድ ስትሄድ እንደ ቀደመው ከደጅ ሆና ለማስተናገድ የባንኩ ሰራተኞች ሲመጡ መስተናገድ የምትፈልገው ከደጅ ሆኜ ሳይሆን ባንክ ቤት ውስጥ ገብቼ ነው የሚል ጥያቄ የቀረበላችው ሰራተኞች ጥያቄው ከነሱ ባላይ በመሆኑ የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ እንዲያናግራት ያስጠሩ ሲሆን መነንም አለች “ባንክ ቤት ውስጥ ገብቼ መስተናገድ ያልቻልኩት ዊልቸር ተጠቃሚ በመሆኔ ሳይሆን ባንኩ ለኔ ምቹ ሁኔታ ባለመፍጠሩ ነው” ከዚህ በኋላ ውስጥ ገብቼ መስተናገድ ፈልጋለው የሚል ሀሳብ ስታቀርብለት የባንኩ ስራ አስኪያጅ እስከዛሬ ድረስ ለተፈጠረው ሁሉ ይቅርታ ጠይቆ ይህ ሁሉ የሆነው ግንዛቤው ስላልነበኝ ነው በማለት በሶስት ቀን ውስጥ ይህንን የመሰል ራምፕ አዘጋጅቶ አካል ጉዳተኞች በባንኩ ውስጥ ገብተ መስተናገድ እንዲችሉ ሆነ፡፡

blog, News

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *